At Equatorial Business Group PLC, our vision is to be the premier trading and supply chain partner for transport, construction and pharmaceutical sectors of Ethiopian economy including exporting Ethiopian products to the world.
Our quality policy is deeply rooted in process approach and continual improvement, compliance with industry best practices, customer-focused, commitment and participation by all employees.
Accordingly, it is our policy that all management and employee shall;
- Commit to ensuring that our products and services consistently meet or exceed the expectations of our customers and applicable requirements.
- Ensure our relationships with external suppliers are built on mutual benefits, aligned with our commitment to delivering products and services that cater to our customers’ needs.
- Strive to foster a satisfying and motivating work environment that encourages employee engagement, development, and accountability in delivering excellence in all aspects of our operations.
- Commit to ensuring our Quality Management System complies with all relevant laws, regulations, directives, and standards set by national, regulatory and statutory bodies.
- Comply with ISO 9001:2015 standards and continually improve the effectiveness of our Quality Management System.
ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በትራንስፖርት፣ በግንባታ እና በመድሐኒት ንግድ ዘርፍ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያን ምርቶች ወደ አለም ገበያ በማቅረብ ዘርፍ ተቀዳሚ የንግድና አቅርቦት ሰንሰለት አጋር የመሆን ራዕይን ይዞ እየተንቀሳቀሰ ያለ ድርጅት ነው።
የጥራት ፖሊሲያችን ቀጣይነት ያለው መሻሻል፤ ሂደታዊ አቀራረብ ፤ የዘርፉን ምርጥ ልማድ የሚከተል፤ ደንበኛ ተኮርና የሁሉንም ሰራተኞች ሙሉ ተሳትፎ መሰረት ያደረገ ነው፤
በዚሁ መሰረት ሁሉም ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሚከተሉትን ተግባራዊ ያደርጋሉ፡
- ምርቶቻችንና አገልግሎታቻችን ከደንበኞቻችን ፍላጎት ጋር የተጣጣሙ ወይም ከፍ ያሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ፤
- ከአቅራቢዎቻችን ጋር ያለን ግንኙነት በጋራ ጥቅም ላይ የተገነባና /የተመሰረተ/ የደንበኞቻችንን ፍላጎት የሚያሟሉ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ካለን ቁርጠኝነት ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ፤
- ሁሉም አገልግሎቶቻችን ላይ የላቀ ብቃት ለማምጣት የሰራተኞችን ተሳትፎ፤ ልማትና ኃላፊነትን በማበረታታት የሚያረካና የሚያነቃቃ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር ጥረት ማድረግ፤
- የጥራት ሥራ አመራር ስርዓትን በሀገር አቀፍ ተቆጣጣሪ እና ሕግ አውጭ አካላት የሚወጡ ሕግጋትን፤ ደንቦችን፤ መመሪያዎችን፣ እና መስፈርቶችን በማክበር ላይ ተመስርቶ የሚተገበር መሆኑን ማረጋገጥ፤
- የ ISO 9001:2015 መስፈርቶችን በማክበር እና ቀጣይነት ባለው የመሻሻል ሂደት ውስጥ የጥራት ሥራ አመራር ስርዓትን ውጤታማነት በቁርጠኝነት ማስቀጠል፤